አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን /AAIC/ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 የተቋቋመ መንግስታዊተቋም ሲሆን  የከተማዋን ቁልፍ ችግሮች ለመፍታትና ዕድገቷን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ ሚና ይኖራቸዋል ተብሎ ከታመነባቸውና እራሳቸውን ችለው እንዲቋቋሙ ከተደረጉት አገልግሎት ሰጪ መ/ቤቶች አንዱ ነው፡፡

የተቋሙ ራዕይ

«በ2022 አዲስ አበባን በኢንቨስትመንት ተመራጭ እና ቀዳሚ በማድረግ የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ሆና ማየት»

የተቋሙን ተልዕኮ

የከተማዋን እምቅ ሃብት በማጥናትና በማስተዋወቅ ጥራት ያለው ኢንቨስትመንትን መሳብ

የተቋሙን እሴቶች

ተጠያቂነት፥ተቋማዊ ኃላፊነት፥ የአገልግሎት ጥራት፥ግልፅና አሳታፊ፥ መልካም ስብዕና ያለው አመራር መፍጠር እና ሌሎችም ጥሩ ስብዕና ያለው ህብረተሰብ መፍጠር

አቶ ግርማ ሰይፉ
የአ\አ\ከ\አስ\ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር መልዕክት

በሀገራችን የልማት እንቅስቃሴውን ለመምራት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ እና እነዚህንም መነሻ በማድረግ የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅዶች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ከተማዋን በ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ከተሞች ተርታ ለማሰለፍ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተነድፈው ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በፈጠሩት አመቺ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በመታገዝም በከተማችን ባለፉት ተከታታይ አመታት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ አዲስ አበባ ከተማም በኢንቨስትመንት መስፋፋት ካላት የተመቻቸ ሁኔታ ማለትም  በከተማዋ የተሻለ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የሰለጠነ እና በቀላሉ ሊሰለጥን የሚችል የተማረ የሰው ኃይል፣ ለወጪና ገቢ ምርቶች ምቹ ሁኔታና ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት መኖርና…….ወዘተ ከሁሉም በላይ ሰላሙ ለኢንቨስትመንት የተመቻቸ ያደርጋታል፡፡

በከተማ ግብርና

አግሮ ፕሮሰሲንግ

ቱሪዝም

ኮንስትራክሽን

የቆዳ ምርቶች

ዜናዎች

INVEST IN
ADDIS ABABA!

Drop Your Questions Here

×