#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢንቨስትመንት ፍቃድ ስረዛ

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ስረዛ

ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሊሰረዝ ይችላል፡፡

 • መረጃ ወይም አፈፃፀም በትክክል በወቅቱ ካልቀረበ ወይም የተሳሳተ ሪፖርት ከቀረበ፤

 • ፈቃዱን በማታለል ወይም በሐሰት መረጃ ያገኘ ከሆነ፤

 • ፈቃዱን ከታለመለት ዓላማ ዉጪ ከተገለገለ፤

 • የኢንቨስትመንት ፈቃዱን በደንቡ መሰረት በወቅቱ ካላሳደሰ፤

 • ፕሮጀክቱ እንደማይጠናቀቅ ከታመነበት

 • በአዋጁ፤ በደንቡ፤ በመመሪያዎች እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸዉን ህጎች ከተላለፈ

 • በተደነገገዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ የኢንቨስትመንት ትግበራ ካልጀመረ፤

 • የእገዳ ምክንያት የሆነዉን ጉዳይ በተሰጠዉ ጊዜ ዉስጥ ካላስተካከለ፤

 • የኢንቨስትመንት ሥራዉን ካቆመ/ከተወ፤

 • የተሰጡትን ማበረታቻ ከታቀደለት/ከታለመለት ዓላማ ዉጭ ካዋለ (በክትትል ክፍልና በቁጥጥር ክትትል መረጃ ከቀረበ)፤

 • ከህግ ዉጪ ለሌላ ሰዉ ካስተላለፈ፤

 • ሁለት አመት ካለፈ ወይም የፕሮጅክቱን ትግበራ ለማጠናቀቅ ከተስማማበት ጊዜ በሁለት አመት ከዘገየ እና በቂ ምክንያት ማቅረብ ካልቻለ፤ የኢንቨስትምነት ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡

INVEST IN
ADDIS ABABA!

Drop Your Questions Here

×