አዲሱ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ ከኮሚሽኑ ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር የሥራ ትዉዉቅ አደረጉኮሚሽነሩ ስናገለግል ከልብ መሆን አለበት!!!ሌብነትን ስም ቀይረን ልናቆለጳጵሰዉ አይገባም ፈጣን ቀልጣፋ አገልግሎት ያለመስጠት ፤ሠዓት ከመሸራረፍ ጀምሮ ሌብነት ነዉ፡፡ስለዚህ ከልብ ሀገራቸዉን እና ህዝባቸዉን ለመጥቀም የሚመጡ ባለሃብቶችን ተገቢ አገልግሎት በተገቢዉ ሰዓት በመስጠት እኛም የምንፈልገዉን ነገር መጠየቅ የምንችልበት መደላድል መፍጠር ይገባናል ብለዋል፡፡በተለይም የደንበኞች አገልግሎት አሠጣጣችን ከፖለቲካ ከብሄር በፀዳ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ሠራተኞዉም ኮሚሽኑ ያቀረቡትን ሀሳብ በመቀበል የአሰራር ማንዋሎች እንዲሻሻሉ የቅሬታ አፈታት ሂደት ዘመናዊ እንዲሆን እና የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ የሚሉ ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡
May
04
2022
0Comment