#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት

በንግድ ማህበር የኢንቨስትመንት ፈቃድ
ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅደመ ሁኔታዎች

 1. የመመስረቻ ጽሑፍ ኦሪጅናልና ኮፒ
 2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ
 3. የሥራ አስኪያጅ ፓስፖርት መጠን ያላቸው ሁለት ፎቶግራፍ
 4. የቲን ሠርተፍኬት ኦሪጅናልና ኮፒ
 5. የሥራ አስኪያጅ ማንነት የሚያረጋግጡ አግባብነት ያላቸው ቋሚ የፓስፖርት ገጾች ወይም የመታወቂያ ካርድ ወይም መንጃ ፈቃድ ቅጅና ኦሪጅናል
 6. በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ
 7. የአገልግሎት ክፍያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)

ለመንግስት የልማት ድርጀት እና የህብረት ሥራ ማህበር
የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅደመ ሁኔታዎች

 1. በሥራ አስኪያጅ ወይም በህጋዊ ወኪል የተፈረመ የኢንቨስትመንት ማመልከቻ ቅጽ (ከቢሮ የሚገኝ)
 2. ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ ወይም ዉሳኔ ቅጅ ወይም የመመስረቻ ጽሁፍ ወይም የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ
 3. በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ
 4. የሥራ አስኪያጅ ፓስፖርት መጠን ያላቸው ሁለት ፎቶግራፍ
 5. የቲን ሠርተፍኬት ኦሪጅናልና ኮፒ
 6. የአገልግሎት ክፍያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)

ለሀገር ዉስጥ ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ
ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

በግለሰብ ባለሃብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅደመ ሁኔታዎች

 1. በባለሃብቱ ወይም በህጋዊ ወኪል ተሞልቶ የተፈረመ የኢንቨስትመንት ማመልከቻ ቅፅ (ከቢሮ የሚገኝ)
 2. ሁለት የቅርብ ጊዜ የፓስፖርት መጠን ያላቸዉ ፎቶግራፎች
 3. በውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድ
 4. የታደሰ መታወቂያ ወይም መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ኮፒ እና ኦሪጅናል፡፡
 5. የአገልግሎት ክፍያ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)

ለዲያስፖራ (ለትዉልደ ኢትዮጵያ) ባለሀብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ
ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

በግለሰብ ባለሃብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅደመ ሁኔታዎች