#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች

ነጻ ማበረታቻ ፈቃድ ቡድን ዋና ዋና ተግባራት

መንግስት የአገሪቱን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ሁለገብ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ከትኩረት አቅጣጫዎቹ አንዱ በዘርፉ የሚሰማሩ የግል ባለሃብቶችን በተለያየመልኩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ተሳትፎአቸውን ማሳደግ ነው፡፡

ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች

የካፒታል ዕቃ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት

ለካፒታል ዕቃ መለዋወጫ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት

የገቢ ግብር እፎይታ ጊዜን ለመጠቀም

የተሸከርካሪን (ፒክ አፕ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት

የካፒታል ዕቃ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት ለአዲስ እና ለማስፋፊያ የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ

 • በአመልካቹ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፅ ከቢሮ ይሞላል

 • በቀጣይ በፕሮጀክቱ የተያዘ ዕቅድ(የሚያስፈልግ ተጨማሪ ዕቃ፣ ስራ የሚጀምርበት ጊዜ ፣ የሚቀጠር የሰራተኛ ብዛት፣ ስራ ላይ የዋለ ካፒታል መረጃ) ካለ የሚያሳይ ቅፅ ከቢሮ ይሞላል

 • የታደስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ (ለአዲስ ፕሮጀክት)

 • ቲን ሰርተፊኬት 1 ኮፒ ለማስፋፊያ ከሆነ የቲን ቁጥር ይሞላል

 • አዲስ ለተገዛው ዕቃ ኢንቮይስ፣ ፓኪንግ ሊስት እና ማስጫኛ ሰነድ 1 ኮፒ (ከአስመጪ ላይ ከሆነ የግዥ ውል 1 ኮፒ)

 • የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ (የፋብሪካ ሕንፃ ተከራይቶም ከሆነ ሕጋዊ የኪራይ ውል) ሰነድ 1 ኮፒ፤ /የባለቤቱ ከሆነ የጋብቻ ሰርተፊኬት/

 • ከዚህ በፊት ለፕሮጀክት የተገዙ ዕቃዎች የተፈቀደበት ሰነድ 1 ኮፒ

 • አመልካቹ በውክልና ወይም በሞግዚት ከሆነ የውክልና ወይም የሞግዚት ህጋዊ ሰነድ 1 ኮፒ

የግንባታ ዕቃ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የድጋፍ ደብዳቤ

 • በአመልካቹ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፅ ከቢሮ ይሞላል

 • የታደሰ ኢንቨስትመንት ፈቃድ፣

 • ቲን ቁጥሩን በማመልከቻ ቅጽ ሞላል

 • አዲስ ለተገዛው ዕቃ ኢንቮይስ፣ ፓኪንግ ሊስት እና ማስጫኛ ሰነድ1 ኮፒ (ከአስመጪ ላይ ከሆነ የግዥ ውል 1 ኮፒ)

 • ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ1 ኮፒ

 • ለዘርፉ የተፈቀደ የግንባታ ፈቃድ 1 ኮፒ

 • በአማካሪው እና/ወይም የግንባታ ፍቃድ በሠጠው መ/ቤት የተረጋገጠ Bill of Quantity በኮሚሽኑ የተዘጋጀ ቅጽ ላይ የተሞላ 1 ኮፒ

 • የግንባታውን ደረጃ የሚገልጽ ሰነድ በአማካሪ ድርጅት ወይም ህጋዊ ዕውቅና ባለው አካል፣

የተሸከርካሪን (ፒክ አፕ ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ

 • በአመልካቹ የተፈረመ ማመልከቻ ቅፅ ከቢሮ ይሞላል

 • በቀጣይ በፕሮጀክቱ የተያዘ ዕቅድ ካለ የሚያሳይ ቅፅ ከቢሮ ይሞላል

 • የታደሰ ኢንቨስትመንት ፈቃድ (ፕሮጀክቱ አዲስ ከሆነ)

 • ቲን ቁጥር በቅጹ ላይ መሙላት

 • አዲስ ለተገዛው ዕቃ ኢንቮይስ፣ ፓኪንግ ሊስት እና ማስጫኛ ሰነድ1 ኮፒ (ከአስመጪ ላይ ከሆነ የግዥ ውል 1 ኮፒ)

 • የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ (የፋብሪካ ሕንፃ ተከራይቶም ከሆነ ሕጋዊ የኪራይ ውል) /የባለቤቱ ከሆነ የጋብቻ ሰርተፊኬት/

 • የካፒታል ዕቃዎች ከውጭ አገር የተገዛበት ኢንቮይስ ወይም ከአገር ውስጥ የተገዙ ከሆነ የሽያጭ ውል/ደረሰኝ 1 ኮፒ እና መሣሪያ ተከላ ስለመጀመሩ ከተረጋገጠ

በተክቶ ማስፈጸም ለመደገፍ መሟላት ያለባቸው ሰነዶች

ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ለመሬትና ማምረቻ ቦታ ድጋፍ ለሚጠይቁ መስፈርቶች

 • በድርጅቱ ባለቤት ወይም በህጋዊ ወኪሉ ስም የተፈረመ ማመልከቻ

 • የታደሰ ኢንቨስትመንት ፈቃድ/ለአዲስ/

 • የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና አንቨስትመንት ፈቃድ/ማስፋፊያ ለጠየቁ/

 • የፕሮጀክት ጥናት

ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክት የመሠረተ ልማት አውታር ድጋፍ ለሚጠይቁ መስፈርቶች

 • በድርጅቱ ባለቤት ወይም በህጋዊ ወኪሉ ስም የተፈረመ ማመልከቻ

 • የኢንቨስትመንት ፈቃድ

 • የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ/ጊዜው ያላለፈ የኪራይ ውል/