ስለ አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኮሚሽኑ

መንግሥት ኢንቨስትመንትን በአጠቃላይ የግል ኢንቨስትመንትን በአገራችን ለማበታትና ለማስፋፋት በ1984 ዓ.ም የመጀመሪያውን የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 15/1984 ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተው ኘሮጀክቶቻቸውን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

ይሁንና አዋጅ ቁጥር 15/1984ን በመተግበር ረገድ ያጋጠሙ ችግሮችን ለማቃለልና የዓለም ተጨባጭ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የውጭ ባለሀብቶች የሚሳተፉባቸውን የሥራ መስኮች በማስፋት እና የሚሰጡ ማበረታቻዎችን ግልጽ በማድረግ ኢንቨስትመንትን በተሻለ ሁኔታ ለማበረታታና ለማስፋፋት አዋጁ በአዋጅ ቁጥር 37/1988 (ከማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር 7/1988 ጋር) በ1988 ዓ.ም እንዲተካ ተደርጓል።

በመቀጠልም በኣገሪቱ ባሉ ክልሎች የሚደረገው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት በ1994 ዓ.ም ያወጣውን የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ለማስፈጸም በሚያስችል መልኩ እንዲመራ የኢንቨስትመንት አዋጁንና የማበረታቻ ደንቡን ማሻሻል በማስፈለጉ አዋጅ ቁጥር 286/1994 እና የማስፈጸሚያው ደንብ ቁጥር 84/1995 እንደ ቅደም ተከተላቸው በ1994 ዓ.ም እና በ1995 ዓ.ም ወጥተው በሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል። የከተማ አስተዳደሩም የቀረጻቸዉን ስትራቴጂዎች እንዲያስፈጽሙ ከተቋቋሙት መስሪያ ቤቶች መካከል የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ሴክተር እንዱ ሲሆን በስሩም የኢንቨስትመንት ኤጀንሲም በ 1995 ዓ.ም ተቋቁሟል።

አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

ኮሚሽኑ የከተማዋን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በባለቤትነት የመምራትና የማስተባበር ተልዕኮውን ለመወጣት እንዲችል የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በቀጣዮቹ ዓመታትም በዋነኝነት  ሰፊ የሰው ሀይል፣ የአገር ውስጥ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት በስፋት በሚጠቀሙ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያደርጉ፣ ወጪ ምርቶችን በስፋት የሚልኩ እና የገቢ ምርቶችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በማተኮር የሚሰራ ነው፡፡

photo_2022-05-04_09-07-32
የተቋሙ

የተቋሙ ራዕይ

«በ2022 አዲስ አበባን በኢንቨስትመንት ተመራጭ እና ቀዳሚ በማድረግ የአፍሪካ ብልፅግና ተምሳሌት ሆና ማየት»

የተቋሙን ተልዕኮ

የከተማዋን እምቅ ሃብት በማጥናትና በማስተዋወቅ ጥራት ያለው ኢንቨስትመንትን መሳብ

የተቋሙን እሴቶች

ተጠያቂነት፥ተቋማዊ ኃላፊነት፥ የአገልግሎት ጥራት፥ግልፅና አሳታፊ፥ መልካም ስብዕና ያለው አመራር መፍጠር እና ሌሎችም ጥሩ ስብዕና ያለው ህብረተሰብ መፍጠር

የተቋሙ ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት

የኮሚሽኑ መዋቅርና አደረጃጀት

አቶ ግርማ ሰይፉ

የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር

MR X

የሕዝብ ግንኙነትና የኦዲዮቪዡዋል ባለሙያዎች

አቶ ማሩ ውብአለም

የዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት

ወ/ሮ ወርቅነሽ ፈይሳ

የሰው ኃብት ዳይሬክቶሬት

አቶ ክብረት መታፈሪያ

የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

አቶ መሰረት ሁንደማ

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ቁጥጥር ቡድን

አቶ ማሩ ውብአለም

የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት

ወ/ሮ ራሄል ይርዳው

አይሲቲ ዳይሬክቶሬት

አቶ ክብረት መታፈሪያ

የጉሙሩክ ነፃ ቀረጥ ማበረታቻ ቡድን

የኢንቨስትመንትጥናት፣ፕሮሞሽንና አንድ ማዕከል ዘርፍ

አቶ ተስፋዬ ጫካ

የ ኢን ቨ ስ ትመን ት ጥናትና ፕሮሞሽ

አቶ ተክልዬ አካሉ

የአንድ ማዕከል አገልግሎት

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ም/ኮሚሽ

አቶ ብሩክ እስተዚያ

የ ኢን ቨ ስ ትመን ት ፕሮጀክ ት ክ ትትል ና ድጋ ፍ ዳይሬክ ቶሬት

ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን

ይጎብኙን!

እርስዎን ለመርዳት እና ማንኛውንም ጥያቄ ለመመለስ እዚህ ተገኝተናል። ከእርስዎ ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን።ቡድናችን ሁሉንም ጥያቄዎችዎን ለመመለስ ደስተኛ ነው።

Reach us through

Social Networks

መልእክት ላኩልን።

INVEST IN
ADDIS ABABA!

Drop Your Questions Here

×