May 04 2022 0Comment

አዲሱ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ ከኮሚሽኑ ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር የሥራ ትዉዉቅ አደረጉ

አዲሱ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ግርማ ሰይፉ ከኮሚሽኑ ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር የሥራ ትዉዉቅ አደረጉኮሚሽነሩ ስናገለግል ከልብ መሆን አለበት!!!ሌብነትን ስም ቀይረን ልናቆለጳጵሰዉ አይገባም ፈጣን ቀልጣፋ አገልግሎት ያለመስጠት ፤ሠዓት ከመሸራረፍ ጀምሮ ሌብነት ነዉ፡፡ስለዚህ ከልብ ሀገራቸዉን እና ህዝባቸዉን ለመጥቀም የሚመጡ ባለሃብቶችን ተገቢ አገልግሎት በተገቢዉ ሰዓት በመስጠት እኛም የምንፈልገዉን ነገር መጠየቅ የምንችልበት መደላድል መፍጠር ይገባናል ብለዋል፡፡በተለይም የደንበኞች አገልግሎት አሠጣጣችን ከፖለቲካ ከብሄር በፀዳ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ሠራተኞዉም ኮሚሽኑ ያቀረቡትን ሀሳብ በመቀበል የአሰራር ማንዋሎች እንዲሻሻሉ የቅሬታ አፈታት ሂደት ዘመናዊ እንዲሆን እና የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ማሻሻያ የሚሉ ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡

ait

Write a Reply or Comment