#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

የኢንቨስትመንት ፍቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አማራጮች በማምረቻ ዘርፎች

አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት

በግለሰብ ባለሃብት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

  • በባለሃብቱ ወይም በህጋዊ ወኪል ተሞልቶ የተፈረመ የኢንቨስትመንት ማመልከቻ ቅፅ (ከቢሮ የሚገኝ)
  • የፕሮጀክቱ ቦታ አዲስ አበባ ዉስጥ መሆን አለበት
  • በእነ ስም/ድርጅት የፈቃድ ጥያቄ ሲቀርብ  የኢንቨስትመንት ፈቃድ አይሰጥም
  • ግለሰቡ ኢንቨስት ሊያደርግ የፈለገውን ካፒታል 30% ፐርሰንቱ ደንበኛ ከሆነበት ባንክ በግለሰቡ አካውንት ላይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሚል ማጻፍ አለበት ወይም የግዥ ደረሰኝ (commercial invoice)  ማቅረብ ያለበት ሲሆን ( መነሻ የኢንቨስትመንት ካፒታል 1.5 ሚሊዮን ብር መታየት ያለበት የመነሻው ካፒታል 30%(450,000ብር) የባንክ ደብዳቤ ወይም የግዥ ደረሰኝ) ደብዳቤው 5 ቀን መብለጥ የለበትም
  • ግለሰቡ ኢንቨስት ሊያደርግ የፈለገውን ካፒታል 30% ፐርሰንቱ ደንበኛ ከሆነበት ባንክ በግለሰቡ አካውንት ላይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሚል ማጻፍ አለበት ወይም የግዥ ደረሰኝ (commercial invoice)  ማቅረብ ያለበት ሲሆን ( መነሻ የኢንቨስትመንት ካፒታል 1.5 ሚሊዮን ብር መታየት ያለበት የመነሻው ካፒታል 30%(450,000ብር) የባንክ ደብዳቤ ወይም የግዥ ደረሰኝ) ደብዳቤው 5 ቀን መብለጥ የለበትም
  • በዉክልና ከሆነ በሠነዶች ማረጋገጫ የተረጋገጠ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ
  •  የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና ለደያስፖራ ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ
  • ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸዉ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
  • በትዉልድ ኢትዮዽያዊያን የሆኑ የውጪ ሀገር ዜጎች ከሆነ (ቢጫ ካርድ ወይም መኖሪያ ፈቃድ)፣
  •  የአገልግሎት ክፍያ ብር1,500.00
  • የሁሉም መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ መቅረብ አለባቸው
  •  

አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሪፖርት

0 +

እቅድ

0 +

ክንው

0 +

በፐርሰንት

አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት

በማህበር የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሲወጣ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

  • በስራ አስኪያጅ  ወይም በህጋዊ ወኪል ተሞልቶ የተፈረመ የኢንቨስትመንት ማመልከቻ ቅፅ (ከቢሮ የሚገኝ)
  • የፕሮጀክቱ ቦታ አዲስ አበባ ዉስጥ መሆን አለበት
  • ማህበሩ ኢንቨስት ሊያደርግ የፈለገውን ካፒታል 30% ፐርሰንቱ ደንበኛ ከሆነበት ባንክ በማህበሩ አካውንት ላይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ለአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሚል ማጻፍ አለበት ወይም የግዥ ደረሰኝ (commercial invoice)  የኢንቨስትመንት ካፒታል 1.5 ሚሊዮን ብር መታየት ያለበት የመነሻው ካፒታል 30%(450,000 ብር) የባንክ ደብዳቤ ወይም የግዥ ደረሰኝ )
  •  
  • በዉክልና ከሆነ በሠነዶች ማረጋገጫ የተረጋገጠ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና ለደያስፖራ ፓስፖርት ፎቶኮፒ
  • ሁለት የፓስፖርት መጠን ያላቸዉ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶ ግራፍ (የስራ አስኪያጅ)
  • በትዉልድ ኢትዮዽያዊያን የሆኑ የዉጪ ሀገር ዜጎች ከሆኑ (ቢጫካርድ ወይም መኖሪያ ፈቃድ)፣
  • በመንግስት የልማት ድርጀት ከሆነ ድርጀቱ የተቋቋመበት ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ
  • የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቲን ነበር ፎቶ ኮፒ
  • የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ ወይም ማህበሩ አዲስ የሚቋቋም ከሆነ የማህበርተኞቹ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
  • የህብረት ስራ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ፎቶ ኮፒ
  • መተዳደሪያ ደንብ እና መመስረቻ ጽሁፍ ላይ የተደረገ ለውጥ ካላ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የጸደቀ ቃለ ጉባኤ ፎቶ ኮፒ
  • የአገልግሎት ክፍያ ብር 1,500

©2022. AIT TECHNOLOGY All Rights Reserved.

INVEST IN
ADDIS ABABA!

Drop Your Questions Here

×