#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

በከተማና በግብርና ዘርፍ

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አማራጮች በማምረቻ ዘርፎች

የከብት እርባታ

የዶሮ እርባታ

በሃገራችን በገጠርም ሆነ በከተማ ውስጥ በስፋት ከሚተገበሩ ዋና ዋና የእንስሳት እርባታ ስራዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የዶሮ እርባታ ስራ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ52 ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ዶሮዎች መካከል አብዛኛውን (ከ95% በላይ) ቁጥር የሚይዙት የሃገረሰብ ዝርያዎች ሲሆኑ፤ የእርባታ ስራምውም የሚከናወነው ባህላዊና ባብዛኛው ጭሮሽን መሰረት ባደረገ ዘዴ ነው፡፡ ከእነዚህም የአካባቢ ዝርያ ዶሮዎች በአመት እስከ 2300 ሜትሪክ ቶን ስጋ እና 78000 ሜትሪክ ቶን እንቁላል ይገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡

የወተት ከብት እርባታና የእንስሳት ማደለብ​ እርባታ

በኢትዮጵያ ያለው የቁም ከብት ብዛት ከፍተኛ መሆኑና በአገር ውስጥና በውጪ ያለው የሥጋ ምርት ፍላጎት እየጨመረ መሄዱ ከብት አደልቦ ለመሸጥ ያለው ያልተተገበረ አቅም ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል:: ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተገኘ መረጃ መሰረት በ2001 ዓ.ም በኢትዮጵያ የነበረው የዳልጋ ከብት፣ የበጎችና ፍየሎች ብዛት እንደ አቀማመጣቸው ቅደም ተከተል 49,297፣ 25,017 እና 21,884 ሚሊዮን ነበረ: ከጠቅላላው ብዛት ውስጥ እንደ አቀማመጣቸው ቅደም ተከተል 55% በትግራይ፣ 93% በአማራና 88% በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይሉ:

የንብ እርባታ

ንብ ማነብ ለምን ይጠቅማል ብንባል ብዙዎቻችን ለማር ምርት፣ ከማር በሚገኝ ገንዘብ ለመጠቀም ከሚሉ ጥቂት ጠቀሜታዎች ውጪ ብዙም ስንጠቅስ አንታይም፡፡ ምክንያቱም በታዳጊ ሃገራት የንብ እርባታ ከማር ማምረት የዘለለ ጠቀሜታ ሲሰጥ አልታየም፡፡ በተወሰነ መልክ ሰም እንደሁለተኛ ምርት ተደርጎም ቢሆን (ማሩ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ እንደተረፈ ምርት ማለት ነው) እፎ አልፎ ጥቅም ሲሰጥ ይታያል፡፡

የፍራፍሬ ምርት

የተጣመረ ግብርና (የእርሻ እና እንስሳት ልማት)
የእንስሳት ሀብት ልማት
የእርሻ ልማት
የደን ልማት

INVEST IN
ADDIS ABABA!

Drop Your Questions Here

×