የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ
ጥር/2018 ዓ .ም
በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባለሐብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ግማሽ ዓመት ብቻ ከ2549 በላይ ባለኃብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ሲሆን ከፈቃድ እና ፈቃድ ነክ አገልግሎቶች ከ20 ሚ ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡
ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራቶች 2549 አዲስ ፍቃድ 162 ማስፋፊያ 188 ማሻሻያ 981 የእድሳት አገልግሎት መስጠቱ የገለጹት ኮሚሽነራ ኮሚሽኑ ለባለሐብቶቹ የኢንቨስትመንት አዋጁ የሚፈቅድላቸው የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያቀረበ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ በዚህ በጀት ዓመት የካፒታል ዕቃ 403 የግንባታ እቃ 46 ተሸከርካሪ 9 መለዋወጫ15 የግብር እፎይታ ለ49 ባለሀብቶች መሰጠቱ ተናግሮዋል ፡፡
አያይዘውም ከቅድመ ትግበራ ወደ ትግበራ ከተሸጋገሩ ፕሮጀክቶች ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ስራ ላይ መዋሉ የገለጹ ሲሆን ከነዚህ ባለሀብቶች ከ4 ሺህ ስልሳ ስምንት በላይ ለሚሆነ ዜጎችም የስራ ዕድል ባለፉት ስደስት ወራት መፈጠሩ አስታውቀዋል።
በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን ወደ ኦን ላይን በማሸጋገር ፤የኢንቨስትመንት ፍሰቱን በማሳደግ፣ የአዲስ አበባ ያላትን እምቅ ሀብት በማስተዋወቅ እና መዲናችን አሁን ያለችበት ቁመና የሚመጥን አገልግሎቶችን በማቅረብ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በቅንጅት የመፍታት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሯ፤ ባለፉት ወራቶች የኢንቨስትመንት ፍሰት እና ጥራት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።